ጠቅላላ

General

አብ ወወልድ

Lyrics

አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስን /2/

አመሰግናለሁ በየዘመን /2/

አንድ ጌታ አንድ አምላክ አንድ አገዛዝ ስልጣን

ከዚህ በቀር ሌላ ምንም አይጨመር

ሦስትነታቸውን በስም በአካል በግብር

ከነዚህ በስተቀር ምንም አይጨመር

በሰማያት ያሉ እልፍ አእላፋት

መናብርት ስልጣናት ሃያላት ሊቃናት

ያመሰግናሉ እያሉ በፍቅር

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር

አመሰግናለሁ የተቻለኝን

እኔም እንደነርሱ ባልመጣጠን

አመድና ትቢያ ስሆን አከበረኝ

ስምህን ለመጥራት ይኸው አበቃኸኝ

ይኸው በዚህ ሰዓት በፊትህ ቆሚያለሁ

በመቅደስህ ዙሪያ ስምህን እጠራለሁ

መንበረ ጸባኦት ትድረስ ምስጋናዬ

ያመሰገንኩትም ትቅረብ በጌታዬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening