✦
ጠቅላላ
•General
ሞት ነው ርሃብ
Lyrics
ሞት ነው ርሃብ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየኝ /2/
ኃይሉ በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን
ጸጋው በእኛ ላይ አድሮ እንበረታለን
ከአንተ ርቀው ሸሽተው እየሄዱ
ጠፋባቸው የጽድቅ መንገዱ
ለስጋዊ ጥበብ ሲፈልጉ
በመታለል ስንቶቹ አንተን አጡ
በተዋህዶ የከበርከው ጌታ
መድሃኒዓለም ሆንክልን መከታ
ስነደክም ሞኞት ሲፈትነን
ሃይልን ሰጥተህ በእጆችህ አዳንከን
የዓለም ሰይፍ በእኛ ላይ ተስሏል
ስጋችንን ሊቆርጠው አድብቷል
ሃይልን ስጠን እንድናሸንፈው
ጸጋህ ለእኛ የዕምነት ጋሻችን ነው
ሐዋርያት ጸጋ በዝቶላቸው
ስለ ፍቅር ፈሰሰ ደማቸው
ዛሬም ለእኛ ጸጋህን አብዛልን
እንዳንደክም ፈተና ሲገጥመን
ጋሻ ሆነህ እንድትመክትልን
ቸር አምላክ ሆይ ወደ አንተ እንጮሃለን
ቢገጥመንም ችግር ወይ መከራ
አትለየን ጌታ ከእኛ ጋራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.