✦
ጠቅላላ
•General
ይለመነናል
Lyrics
ይለመነናል አምላክ አብርሃም
ይታደገናል መድሃኒዓለም
ለፍጥረታት ሁሉ እጁን የዘረጋ /2/
ቸር እረኛ ነው አልፋና ኦሜጋ /2/
አብርሃም ይስሐቅን ያዕቆብን አስበህ
የማልክላቸውን ቃል ኪዳን አስታውሰህ
ደካማ ለሆነው ስጋ ሰልጥኖብን
አትመልስ ጌታ የምህረት ዓይንህን
ከሰማየ ሰማይ ይድረስ ጩኸታችን /2/
እንዘን እናልቅስ ስለበደላችን /2/
ባይመለከተን አምላክ አብርሃም
በምህረት ዓይኖቹ መድሃኒዓለም
ባይዘረጋልን አምላክ አብርሃም
የፍቅር እጆቹ መድሃኒዓለም
ሕዝበ እስራኤል ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ /2/
አድኖናልና በሚያስደንቅ ፍቅሩ /2/
ምንም እንኳን ክህደት ቅጥፈት ቢበረታ
ስለ አብርሃም ብለህ አልተውከንም ጌታ
ለቅዱሳን ያለህ ቃል ኪዳን ሲጸና
ቀስተ ደመናህን አይተነዋልና
የእስራኤል አምላክ የማታንቀላፋ /2/
በፍደቅርህ ታደገን በሞት ሳንጠፋ /2/
ቃል ኪዳኑ ግሩም አምላክ አብርሃም
ምህረቱ የበዛ መድሃኒዓለም
ርስት ጉልታችን አምላክ አብርሃም
የህይወታችን ቤዛ መድሃኒዓለም
ሳይጸየፍ ጌታ ያደፈ ሃጢያቴን /2/
ከማጥ ውስጥ አወጣኝ ታደጋት ሕይወቴን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.