✦
ጠቅላላ
•General
ባለጸጋ እመቤት
Lyrics
ባለጸጋ እመቤት ባለጸጋ እናት
አፍሰናል ከደጅሽ ብዙ በረከት
ወጀቡን ቀዝፈናል ብለን ማርያም
እንዘምራለን እስከ ዘለዓለም
ሰው በሌለበት ከተማ ሞት በከበበው ጨለማ
ሞገስ ገንዘቤ ዘመዴ በምልጃሽ ቀንቷል መንገዴ
ፋና ሆነሽኝ መብራቴ በክብርሽ ደምቆልኝ ቤቴ
ሐሴት አረኩኝ ደስታ ያዘነው ገጼ ተፈታ
እንደኔ ሃጢአት በደል ይገባኝ ነበር መስቀል
ጽኑ ኪዳኗ ጋረደኝ እምባ ጸሎቷ ታደገኝ
እስኪ ልናገር ስራዋን የምህረት እናት መሆኗን
ጽዮን እጆቿን ዘርግታ አስታርቃኛለች ከጌታ
የክብር ሰንደቅ አርማዬ ወደ መቅደሱ መግቢያዬ
አንቺን ይዤአለሁ ጠባቃ የሞቴ ታሪክ አበቃ
እልል እላለሁ ከልቤ ልቅሶዬ ሰምሮ ሃሳቤ
ድንግል ፍቅር ናት ሰላም ለክብሯ ይስገድ ዓለም
የእልፍኜ ማማር ውበቴ ትሩፋቴ ነሽ ሙላቴ
ስምሽ መቀነት ሆኖኛል የዛለው ክንዴ በርትቷል
ባማረው ቤትሽ አድጌ በልጅሽ ፀጋ በልጽጌ
በእናትነትሽ በረከት ይኸው ቆሜያለሁ በሕይወት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.