ጠቅላላ

General

መንግስተ ሥላሴ

Lyrics

አማን አማን /2/

መንግስተ ሥላሴ ዘለዓለም /2/

ንግበር ሰብዓ ብለው አማን በአማን

አዳምን ፈጥረውት አማን በአማን

በቸርነትና በፍቅር ጎበኙት

ሁሉን በእጁ አርገው ሁሉን አስገዙለት

የፍቅር የደስታ አማን በአማን

የበረከት አባት አማን በአማን

መንግስቱ ዘለዓለም ህልፈት የሌለበት

በአፈ መላዕክት የሚመሰገኑት

የዛን የደግ አባት አማን በአማን

የአብርሃምን ቤት አማን በአማን

እንደባረኩለት የእኛንም ባርኩልን

የቤታችን ዋልታ መሰረት ሁኑልን

በመከራ ጊዜ አማን በአማን

ከጭንቅ የሚያወጣ አማን በአማን

ስምህን ሳመሰግን ትረካለች ነፍሴ

የነሙሴ አባት የአብርሃሙ ስላሴ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening