ጠቅላላ

General

መጠጊያዬ

Lyrics

መጠጊያዬ ክብሬ ትምክህቴ

ማረፊያዬ የዘላለም ቤቴ

እናቴ ነሽ ዋሴ ለሕይወቴ

መጠጊያዬ ግሩም የአምላክ ስራ

ሁላችን በአንድነት ከሃጢያት ከመቅሰፍት

በዓለም ፍቅር ተስቤ ስማረክ

ከጽድቅ ተለይቼ ብቻዬን ስለጉድ

ፍጻሜዬ ሁሉ ላያምር

ለማይጠቅመኝ ነገር እንዲሁ ስኖር

ሽቶ መዓዛዬ በአንቺ ነው የሚያምር

የልቤን ታውቂያለሽ ያሰብኩትን

ምኞቴን በሙሉ በነብስ ያለምኩትን

በልቤ ውስጥ ይድረስ በረከትሽ

ባንቺ ተመክቼ እንዳልጠፋ ልጅሽ

በብርሃነ መስቀል ልዳሰስ በእጅሽ

ወደ እርሱ ለመቅረብ ተስኖኛል

ሃጢያቴ ድጥ ሆኖ ዘወትር ይጥለኛል

እስከ መቼ ድረስ ከእርሱ ልለይ

መድሃኒት ከሌላ ከየትም አላገኝ

ድንግል ንጽህናሽ ለእኔ ሆኖ ይገኝ

እናቴ ርህሩህ ነሽ እጅግ አዛኝ

በአማላጅነትሽ በኪዳንሽ ልዳኝ

በዛች በፍርድ ሰዓት ፈጣሪዬ

ከእኔ ራቂ እንዳይል አዝኖብኝ ጌታዬ

ድጋፍ አንቺ ሁኚኝ መከታዬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening