✦
ጠቅላላ
•General
ያዕቆብ ከቤርሳቤት
Lyrics
ያዕቆብ ከቤርሳቤት ወደ ካራን ሲሄድ
የለውም ነበረ አማካሪ ዘመድ
ፀሐይ ጠልቃ ነበር ከዛ እንደ ደረሰ
ከእርሱም በታች ድንጋይ ተንተራሰ
ህልምንም ዓለመ ታላቁን ራዕይ
መሰላል ተተክሎ ከምድር እስከ ሰማይ
ሲወጡ ሲወርዱ መላዕክት በእርሱ ላይ
እግዚአብሔርም ቆሞ ከላይ ከጫፏ ላይ
የአባቶችህ አምላክ እኔ እግዚአብሔር ነኝ
ይህን ምድር ለርስትህ እሰጥሃለሁኝ
ዘርህ እንደ አሸዋ በምድር ይበዛል
በአራቱም ማዕዘን ህዝብህም ይዘራል
አበው በምሳሌ እንደተናገሩት
ከምድር እስከ ሰማይ አምላክ የዘረጋው
በላይዋ ተቀምጦ በግልፅ የታየባት
የያዕቆብ መሰላል እመቤታችን ናት
ሰማይና ምድር የሚታረቁባት
ወልደ እገዋለ እምያው የተወለደባት
መላዕክት ከሰማይ በአንድ የዘመሩባት
ታካቋ መሰላል እመቤታችን ናት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.