ጠቅላላ

General

ስላሴ ዘከሃ

Lyrics

ስላሴ ዘከሃ ስላሴ ዘዝየ /2/

ሁልጊዜ እለዋለሁ አምላኬ አምላኬየ

ዓይኔን ወደ ተራራው አነሳለሁና

እረዳቴ የኔ ስላሴ ነውና

አምባ መጠጊያዬ እኔ በአንተ አላፍርም

የማዳንህ ስራ ዛሬም ቢዘገይም

የጠላት ፍላጻን ሰብሮ ታድጎኛል

ማን እንደ ስላሴ እረዳት ሆኖኛል

ወዶኛል አዳነኝ እግዚአብሔር ክፍሌ ነው

ቀብቶኛልና እኔ አመልከዋለው

እረኛዬ እግዚአብሔር እኔን ቀብቶኛል

በለመለመ መስክ ሁሌ ያሰማራኛል

ከነጣቂ ተኩላ ይኸው ሰውሮኛል

ለማመስገን በቃሁ እርሱ ፈቅዶልኝ

አንተ ለእኔ ጌታ መሸሸጊያዬ ነህ

ከጣርም ከጭንቀትም ትጠብቀኛለህ

እንዲታደጋችሁ ስላሴን ፈልጉት

ስሙንም በአንድነት ከፍ ከፍ አድርጉት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening