✦
ጠቅላላ
•General
አወድሰኝ ኤፍሬም
Lyrics
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርከኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምስጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደረሰው ገባና
ልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ
ዳግማዊት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እርሱ ፈቀደ
የሰማይ ምስጢር በማህጸንሽ ተከናወነ
ከዘሩ ቀርተሽ በንጽህናሽ የሰው ዘር ዳነ
ሰዓሊለነ /2/
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
በሔዋን ምክንያት በለስዋን በልተን ገነት ቢዘጋ
በአንቺ አማላጅነት ደግሞ ተዛመድን ከአምላካችን ጋር
ትውልድ ሁሉ በክብር አመሰገነ
የሲኦል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ
ሰዓሊለነ /2/
ሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል
እግዚአብሔር መርጦሽ በማህፀንሽ ዙፋኑን ተክሏል
የዲያቢሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ
በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ
ሰዓሊለነ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.