ጠቅላላ

General

እነሆ አዲስ ሰማይ

Lyrics

እነሆ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር አየሁ /2/

ፊተኛው አልፎ በዚያ እኖራለሁ /2/

የተሸከመችው መኖሪያ ቤቴ

ያጌጠችው ድንኳን መክበሪያ ሀብቴ

እግዚአብሔር ለልጁ ለእኔ ያዘጋጃት

አዲሲቱ ሰማይ ኢየሩሳሌም ናት /2/

ዓለም ሳይፈጠር ጌታ ያሰናዳት

ማርና ወተት ያልተቋረጠባት

የጎደለ ነገር እንከን የሌለባት

የዘላለም ቤቴ ኢየሩሳሌም ናት /2/

ምንም አልጨነቅ ለሚቀረው ነገር

ልክ እንደ ትላንቱ ነገንም ለማይኖር

ሁሉም ከንቱ ሲሆን ከፀሐይ በታች

የእግዚአብሔር ክንድ ግን ሁሌም የሚመች /2/

አስራ ሁሉት ደጆች የተሰሩላት

የሐዋርያት ስሞች የተጻፉባት

መቅደሷ በጉ ነው ሁሉን የሚገዛ

የዘለዓለም ንጉስ ምህረቱን ያበዛ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening