ጠቅላላ

General

ሰዓሊለነ ቅድስት

Lyrics

ሰዓሊለነ ቅድስት እንልሻለን /2/

እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን

ለምኝልን እመቤታችን /2/

ተስፋ አንቺ ነሽና ለፍጥረት ዓለም

እየተመኩብሽ እስከ ዘለዓለም

ሃጢያታቸው ተደምስሶላቸው

በአንቺ ጸሎት ዳነች ሕይወታቸው /2/

ስምሽም ስልጡን ነው በእግዚአብሔር መንበር

ቃል ኪዳን ገባልሽ ልጆችሽን ሊምር

በአንቺ ጸሎት ይተማመናሉ

ጠዋት ማታ ቅድስት ሆይ ይላሉ /2/

ዓለም ስትዋጋን በምኞት ስለት

ነፍሳችን ስትደክም ሲከባት ሃጢያት

መንገድ ጠፍቶን ግራ ሲገባን

ብርሃናችን ነይ እናታችን /2/

የልባችን ሀዘን እጅግ ከብዶብናል

ከበለሱ በታች በፍርሃት ወድቀናል

እንደ ኤልሳቤጥ እንደ ዘመድሽ

ደስ አሰኝን ይሰማን ድምፅሽ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening