✦
ጠቅላላ
•General
ፍቅሩን ለገለጸው
Lyrics
በመስቀል ተሰቅሎ ፍቅሩን ለገለጸው
ምን ስጦታ አለን ለእርሱ የምንከፍለው
ምስጋና ነውና ከእኛ የሚፈልገው
ቸር አምላካችንን ተመስገን እንበለው
ዓለም እስኪደነቅ ድንቅ አድርጎልናል
እንዲሁ ያለዋጋ ጸጋውን ሰጥቶናል
ትናንት ለእስራኤል ሞገስ የሆናቸው
ስሙን እናመስግን ዛሬም ከእኛ ጋር ነው
አፋችን ይሞላ በታላቅ ምስጋና
ከሃጢያቱ ባህር ተሻግረናልና
ክቡር ምስጉን አምላክ ቅዱስ እንበለው
ኢሳይያስም በክብር በራዕይ እንዳየው
ከቶ ለእግዚአብሔር ምን ይከፈለዋል
ሁሉም የራሱ ነው ማን ምን ይሰጠዋል
አመስጋኝ ቢቀኝም ክብር ለራሱ ነው
እርሱ በባህሪው ዘለዓለም ምስጉን ነው
ሙሴም ዝም አላለ ዳዊትም አልተኛ
በጎቹ ዘመሩ ለመልካሙ እረኛ
ያሬድ ተመሰጠ ወደ ሰማይ ዓለም
እኛም ከእርሱ ጋር እንዘምር ዘለዓለም
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.