✦
ጠቅላላ
•General
የሐይማኖት ፍሬ
Lyrics
ተነግሮ የማያልቅ ነው ጸጋህ /2/
በጸሎት የተጋህ የሐይማኖት ፍሬ
ተክለሃይማኖት የዕምነቱ ገበሬ
በወንጌል ብርሃን ህዝብህን የመራህ
የሃጢያትን ባህር ከፍለህ ያሻገርክ
ኢትዮጵያዊው ሙሴ በመስቀልህ ባርከን
ፍሬ እንድናፈራ ንፁህ ዘር አድርገን
ሐዲስ ሐዋርያ አባ ተክለሃይማኖት
ወንጌልን ያስተማርከን ለክርስቶስ መንግስት
ጸበልህ እንዲምረን ውረድ አባታችን
በዕጣንህ መዓዛ ይፈወስ ደዌያችን
ለማጠን የበቃህ የስላሴን መንበር
ሰይጣን ከቶ የማይደርስ በሄድክበት ሀገር
ለህሙማን ሁሉ የሆንካቸው ፈውስ
ጠብቀን ተክልዬ በስጋም በነፍስ
በጣሙን የበዛ ትሩፋት ምግባርህ
ጸሎትህን ያልተውክ ቢቆረጥ አነድ እግርህ
ምዕራፈ ቅዱሳን የወንጌል ገበሬ
እኛንም አድነን ከዚህ ዓለም አውሬ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.