✦
ጠቅላላ
•General
አልፈርድም እኔ
Lyrics
አልፈርድም እኔ በማንም በደል በማንም ሃጢያት
በፈረድኩበት እንዳልመዘን ጌተ ሲመጣ በሃይል በስልጣን
በቸርነቱ አምላክ ባይተወው በደሌን ሁሉ
ውስጤ ቢፈተሽ በተሰጠኝ ህግ በቅዱስ ቃሉ
በምን ምግባሬ በሰው እፈርዳለሁ ዓይኔን አቅንቼ
በደሌ በዝቶ ለራሴ ሳላውቅ ለሃጢያት ሞቼ
ይልቅ የአንዱን ሸክም ሌላው ሰው አዝሎ መጓዝ ይችላል
መፍረድ ከመጣ አንድም ሰው አይድን ሁሉም በድሏል
ወንድም ወንድሙን እየከሰሰ ለፍርድ አቁሞ
አህዛብ ያያል በንትርኩ እጅግ ተገርሞ
ክርስትያን ሆኖ ከወንድሙ ጋር እየተጣላ
ዓለም ዳኘችን በጸብ ፍርድ ቤት ታረቁ ብላ
ክርስትያን ሆነን በአህዛብ መሃል እየተካሰስን
አምላክ አዘነ የመስቀሉን ዓላማ ትተን
መቼ ከሰሰ የከሰሱትን የገረፉትን
አይተናል እንጂ ለጠላቶቹ ምህረት ሲለምን
በጽድቅ ስራ ላይ ለእውነት ብለን መጥተናል እንጅ
ማን ነው የሾመን በወንድሞች ላይ አርጎ ፈራጅ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.