ጠቅላላ

General

እንደ ኤልሣቤጥ

Lyrics

እንደ ኤልሳቤጥ ላመስግንሽ

ፊትሽ ወድቄ ልሳለምሽ

የጌታዬ እናት የእኛ አማላጅ

አዛኝ ነሽ ከልብ ፍጹም የዋህት

እርህራሄሽ ያስደስተኛል

ስለ ሃጢያቴ ምልጃሽ ይቀድማል

የሰላምታሽ ድምፅ ደስ ያሰኘኛል

ከትካዜዬም ያሳርፈኛል

ድምጽሽ ሲሰማኝ ልቤ ይረካል

ሀዘኔ ቀርቶ ፊቴ ይፈካል

በእናትነት አንቺን ለሰጠኝ

ቸሩ አምላካችን ይክበር ይመስገን

የሁሉ እመቤት የሁሉ አጽናኝ

የአበው መድሃኒት ከአምላክ አገናኝ

ዛሬም በልቤ ደስት ጨምረሽ

እንደ ኤልሳቤጥ ሰላም ልበልሽ

ከሴቶች መካከል መርጦ ቀድሶሻል

ትውልድ ሁሉ ብጽኢት ይልሻል

በልዩ ውዳሴ ያመሰግኑሻል

ድንግል እናታችን በቀኙ ቆመሻል

የሰላምታሽን ድምፅ ልቤ ሲሰማ

ነፍሴ ደስ አላት ቀለለ ሸክሟ

ድንግል ለክብርሽ ስንበረከክ

እጅሽ ይዘርጋ ለመባረክ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening