ጠቅላላ

General

እስከ መቼ ነው

Lyrics

እስከ መቼ ነው የማልለወጠው

ባልተሰበረ ልብ የምመላለሰው /2/

በሰጠኸኝ ጸጋ ድካሜ ተከድኖ

ዓለም ይከበኛል አልቆና አግኖ

ይህን ከንቱ ወጥመድ ጣለው ከኋላዬ

ትንሽ ሰው መሆኔን ይወቅ ህሊናዬ

ፀሐይ ስትጨልም ከዋክብት ሲረግፉ

ለገናናው ክብርህ ፈቅደው ሲሸነፉ

ለሁለት ሲከፈል ድንጋያማው ዓለት

የእኔ ልብ መቼ ይሆን የሚሸነፍለት

ቃልህን ስሰማ ልቤን ይነካዋል

ጽድቅን አስባለሁ ሀዘን ይሰማኛል

ወዲያው ተመልሼ ሁሉን እረሳለሁ

ለዚህ ዓለም ስብከት ልቤን እከፍታለሁ

መኖርን እሻለሁ ልቤ ተለውጦ

አንተን እንዲያከብርህ ከሁሉ አብልጦ

ዓለት አይሁን ይቅር ይሰበር ከፊትህ

ደንግጬ እነድመለስ ሲገስጸኝ ድምፅህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening