ጠቅላላ

General

ስራው ድንቅ ነው

Lyrics

እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው /2/

ለእኔ ያደረገው ብዙ ነው /2/

እግዚአብሔር ስራው ድንቅ ነው /2/

ለእኔ ያረገልኝ ብዙ ነው /2/

እረዳቴ እርሱ ነው ከሰማያት

እግዚአብሔር ጠባቂ ለእኔ ሕይወት

ብርሃኑን በፊቴ የሚያበራ

አምላኬ ድንቅ ነው የእርሱ ስራ

በመንገዴ ሁሉ የሚመራኝ

ስነሳም ስወድቅም የሚያስበኝ

ማንም አልመጣልኝ ከወገኔ

ከሁሉም ይበልጣል እርሱ ለእኔ

የዕዳዬን ደብዳቤ ውድቅ አድርጎ

ሕይወቴን መራልኝ ወደ በጎ

ኸረ እንደ እግዚአብሔር ማን ይሆናል

እርሱን ለሚፈሩት ይታመናል

አንድ ቀን አስቤ ተጨንቄ

ለመኖር አልቻልኩም ተጠንቅቄ

ሁሉን ነገር ለእርሱ ትቼዋለሁ

በምህረቱ ጥላ እኖራለሁ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening