ጠቅላላ

General

በረከትህ ይደር

Lyrics

በረከትህ ይደር /2/ በሁላችን

የዝማሬ ጸጋህ ዳዊት አባታችን

ምስጋና እንድንሰዋ እኛም ለአምላካችን

በገና የያዙበት እጆቹ ጠንክረው

ጎልያድን ጣሉት ጠጠርን ወርውረው

ከበሮ የመታበት ክንዶቹ በርትተው

አንበሳን ገድለዋል ግልገል ከአፉ ነጥቀው

ክፉ መንፈስ ከሰው የሚያስወግደው

የሳኦልን ህመም የሚፈውሰው

የበገና ምስጢር የዝማሬ ቃና

በእኛም ይደርብን ልጆችህ ነንና

እልል /2/ በሉ እንድታሸንፉ

ድምጽንም አሰሙ ቅጽሩን እንድታልፉ

የመዝሙር ነጎድጓድ ወህኒውን ይከፍታል

ብርሃናዊው መላዕክ ከሰማይ ይመጣል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening