ጠቅላላ

General

ከንቱ ነኝ

Lyrics

ከንቱ ነኝ የከንቱ ከንቱ ነኝ

ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ

ተስፋዬ የሚሆነኝ ሕይወት የሚሰጠኝ

እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ

አምላኬ ብቻ ነው የሚያስተማምነኝ

እኔ ንጉስ ነበርኩ በክብር ያጌጥኩኝ

ሁሉን በምድር ላይ በጥበብ ፈፀምኩኝ

የዚህ ዓለም ደስታ ምንም አላዋጣኝ

በመጨረሻ ግን በሞት ተወሰድኩኝ /2/

ከጸሐይቱ በታች አዲስ ነገር የለም

ሰዎች ይደክማሉ እስከ ዘለዓለም

ጥበብን ፍለጋ ደክሜ ነበረ

ሁሉም ከንቱ ሆኖ በመቃብር ቀረ /2/

ከእኔ አስቀድመው የከበሩ ሁሉ

አፈር ተጭኗቸው ከመቃብር አሉ

እብደትና እውቀት ሁሉን አወቅኳቸው

ምንም ቋሚ የለም ሁሉም ከንቱ ናቸው /2/

ልቤን የሰጠሁት ተስፋ ያደረኩት

አልጨበጥ ብሎኝ አለሁኝ ስታክት

የጥበብም ብዛት ለትካዜ ሰጠኝ

እኔ በዚህ ዓለም እጅግ ጎስቋላ ነኝ /2/

ልቤንም ፈተንኩት በደስታ ብዛት

የዚህን ዓለም ለውጥ ጣዕሙን አቀመስኩት

ሳቅም በልቤ ውስጥ ይፍለቀለቅ ነበር

ሁሉም ከንቱ ሆኖ ገብቶ ከመቃብር /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening