ጠቅላላ

General

ተስፋችን ነህ አንተ

Lyrics

ተስፋችን ነህ አንተ እስከ ዘለዓለም /2/

የድንግል ማርያም ልጅ መድሃኒዓለም /2/

ደምህን አፍስሰህ ስጋህን ቆርሰህ /2/

ብሉ ጠጡ ብለህ ለዓለም ሰጠህ /2/

የዘለዓለም ሕይወት እንድናገኝ ሆነ /2/

በመድሃኒዓለም ሁሉም ተከወነ /2/

ደሙን የረጨኸው ቅዱስ ዑራኤል /2/

ኢትዮጵያን ቅረባት ትሁን ባለሟል /2/

በደሙ ተባርካ በዑራኤል እጅ /2/

ዛሬም ከእርሷ ጋር ነው ሆኗት አማላጅ /2/

ጸሎትህ ኢትዮጵያን እጅግ ቀደሣት /2/

ሃያሉ ዑራኤል መቼም አይተዋት /2/

የሰው ልጅ ችግር ከሚያስወግድ መላክ /2/

አንዱ ዑራኤል ነው ምድራችንን ይባርክ /2/

ይመስገን ቸር አምላክ

አሜን /2/ ይሁን አሜን ሃሌ ሉያ /2/

ሰላምን ለግሣት ለኢትዮጵያ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening