✦
ጠቅላላ
•General
ምስጋና ነው ስራዬ
Lyrics
ምስጋና ነው ስራዬ በዘመኔ በእድሜዬ
ለዋለልኝ ውለታ ምን ልክፈለው ለጌታ
ትላንትና ጥልቁ ነበረ መኖሪያዬ
የማዳኑ ቀኑ ደረሰ የጌታዬ
እራቁቴን ሸፍኖልኛል በብርሃኑ
ምግቤ ሆኗል ስሙን ማወደስ በየቀኑ
አልተራብኩም አልተጠማሁም በዘመኔ
ምግበ ስጋ ምግበ ነፍስ ነው ጌታ ለእኔ
ተበጥሷል የእሳቱ ገመድ ሰንሰለት
አልረሳውም የእርሱን ውለታ ብድራት
ማን ያፈቅራል እስከ ሞት ድረስ ዋጋ ከፍሎ
ማን ያድናል ባለስልጣኑን ሞትን ገድሎ
አማኑኤል በፍቅሩ ጸዳል ምድርን ከድኖ
ስው አድርጎኛል የማይሆኑትን ሁሉ ሆኖ
እንዴት ብዬ ፍቅሩን ልግለጸው እንዴት ብዬ
ስለ እጆቹ በእንባ ጨቀየ መኝታዬ
በእርሱ ቁስል ነፍሴ ወጥታለች ከመከራ
በዝማሬ ስሙን ማክበር ነው የእኔ ስራ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.