ጠቅላላ

General

አበባየሆሽ

Lyrics

እሰይ ደስ ደስ ይበላችሁ /2/

ቅዱስ ዩሐንስ መጣላችሁ

ደስ ደስ ይበላችሁ

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን /2/

ጌታ አለ ብለን

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን /2/

ድንግል አለች ብለን

ቅድስት /2/ አበባየሆሽ

ባልንጀሮቼ አበባየሆሽ ቁሙ በተራ አበባየሆሽ

በጎ ምግባርን አበባየሆሽ በዕምነት እንስራ አበባየሆሽ

ዛሬ ነው ቀኑ አበባየሆሽ መመለሻችን አበባየሆሽ

ይቅር እንዲለን አበባየሆሽ ቸሩ አምላካችን አበባየሆሽ

አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ አበራ /2/

ድንግል ማርያምን ቅድስት እንለምናት

ምህረት የሚሰጥ ቅድስት ቃል ኪዳን አላት

ጭንቀት ይርቃል ቅድስት ይቀርባል ሰላም

በህገ ልቦና ቅድስት ስሟ ሲጠራ

የድንግል ማርያም ቅድስት

አደይ የብርሃን ጮራ በኢትዮጵያ አበራ /2/

ፈጣሪን አውቀሽ ጥንቱን ህገ ነብያትን ጥንቱን

ከዓለም ቀድመሽ ተቀበልሽ ጥንቱን

በብሉይ ኪዳን ለጌታ መስዋዕት አቀረብሽ ለጌታ

ተስፋ ካረጉት ከአይሁድ ህገ ወንጌልን ከአይሁድ

በፊት ይዘሽ ተገኘሽ በፊት

ኢትዮጵያ ደስ ይበልሽ ትልቅ ጸጋ አለሽ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening