✦
ጠቅላላ
•General
የዓለምን በደል
Lyrics
የዓለም በደል የሰውን ግፍ አይቶ
ዘጠና ዘጠኙን መላዕክት ትቶ
ጽድቅን ለመፈፀም በደልን አጥፍቶ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ
የሰማያት ሰማይ የማይችለው ንጉስ
ተወለደ ተጠመቀ እኛን ለመቀደስ
ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ
ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ
ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ
እንደ ተናገረ ዳዊት በትንቢቱ
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ
ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቅን ሲመሰርት
መጣ በደመና ሰማያዊው አባት
እየመሰከረ የልጁን ጌትነት
የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ
አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለእኛ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.