✦
ጠቅላላ
•General
ወደ ማደሪያው
Lyrics
ወደ ማደሪያው ገብቼ ልስገድ ለእግዚአብሔር
ምስጋናን ላቅርብ ስለ ስሙ ክብር
አድርጎልኛልና አመሰግነዋለሁ
በአፀደ መቅደሱም እሰግድለታለሁ
ከፊቱ ለመቆም ማልጄ እነሳለሁ /2/
በመከራዬ ቀን ሆኖኛል መከታ
ቤቱም ተገኝቼ በፍጹም ደስታ
የከንፈርን ፍሬ ልሰዋ በእልልታ /2/
አስር አውታር ባለው በበገና
በመላዕክቱ ፊት ለማቅረብ ምስጋና
የአፌንም ነገር ሰምተኸኛልና /2/
ለስሙ ልንበርከክ ለእርሱ እንደሚገባ
ስዕለትን ልፈጽም ላቅርብለት መባ
ወደ አደባባዩ በምስጋና ልግባ /2/
አሸበሽባለሁ ድምፄን አሰምቼ
በቤተመቅደሱ ሌሊት ተገኝቼ
እንደ ካህናቱ እጆቼን ዘርግቼ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.