✦
ጠቅላላ
•General
መመኪያዬ ርስቴ
Lyrics
መመኪያዬ ርስቴ የሆነች
ድንግል ማርያም ለእኔ እናቴ ነች
እናቴ ነች /3/
ስማጸናት ትመጣለች እናቴ ነች
ወዳጄ ሆይ ትለኛለች እናቴ ነች
መድሃኒቴ ስለሆነች እናቴ ነች
የድህነት ምክንያት ነች እናቴ ነች
የመስቀል ስር ስጦታዬ እናቴ ነች
እመቤቴ ከለላዬ እናቴ ነች
ወልደ አምላክ ምህረት ይዛ እናቴ ነች
መጣችልኝ የእኔ ቤዛ እናቴ ነች
በጌታ ቀኝ የምትቆመው እናቴ ነች
ላመናት የምትቀርበው እናቴ ነች
ንጽህት ቅድስት የሆነች እናቴ ነች
የዓለም ንግስት እናቴ ነች
ድንግል ማርያም መመኪያዬ እናቴ ነች
አክሊሌ ነች አለኝታዬ እናቴ ነች
መንግስተ ሠማይ መግቢያዬ እናቴ ነች
የምቀርበው ከጌታዬ እናቴ ነች
ባንቺ እኮ ነው እመቤቴ እናቴ ነች
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.