ጠቅላላ

General

እሰይ እልል በሉ

Lyrics

እሠይ እልል በሉ ተገኘ መስቀሉ /2/

የጥል ግድግዳ አበባ የፈረሰበት አበባ

ሰው ከእግዚአብሔር ጋር አበባ የታረቀበት አበባ

የእግዚአብሔር ልጅ አበባ የነገሰበት አበባ

የሞት አበጋዝ አበባ የወደቀበት አበባ

አይሁድ በቅናት አበባ መስቀሉን ቀብረው አበባ

ቢከድኑት እንኳን አበባ በቆሻሻቸው አበባ

ጌታን መቃወም አበባ ስለማይችሉ አበባ

ይኸው ተገኘ አበባ ወጣ መስቀሉ አበባ

ደጉ ኪረኮስ አበባ ሽማግሌው አበባ

እሌኒን መራት አበባ በደመራው አበባ

ጌታ በእርሱ ላይ አበባ በመስቀሉ አበባ

ጭሱ ሰገደ አበባ ወደ መስቀሉ አበባ

የዕምነት ምልክት አበባ መስቀል ነውና አበባ

ተራራው ሜዳ አበባ ሆነ እንደገና አበባ

እንደተነሣ አበባ ጌታን እንደካዱ አበባ

ነጎድጓድ ወጣ አበባ ከእጸ መስቀሉ አበባ

እኛም በመስቀል አበባ እንመካለን አበባ

በእግዚአብሔር ጥበብ አበባ መች እናፍራለን አበባ

ሞኝነት እንኳን አበባ ቢሆን ለዓለም አበባ

ኃይል እጸወነ አበባ ለዘለዓለም አበባ

ግድግዳው ፈርሷል አበባ የልዩነቱ አበባ

ምድርና ሰማይ አበባ ሆነ እንደጥንቱ አበባ

ነፍስና ስጋ አበባ በእርሱ ታርቀዋል አበባ

ህዝብና አህዛብ አበባ ወንድም ሆነዋል አበባ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening