ጠቅላላ

General

የመስቀሉ ፍቅር

Lyrics

የመስቀሉ ፍቅር ሲገባቸው /4/

እመቤታችንን እናያታለን

የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው /4/

እመቤታችን አለች ከጎናቸው /4/

አባ ህርያቆስ አባታችን

የመስቀሉ ፍቅር ቢገባው

ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር

ከእመቤቴ ጋር ሲነጋገር

ከድንግል ማርያም ጋር ሲነጋገር

ነይ ነይ እምዬ ማርያም

ነይ ነይ ቤዛዊት ዓለም

አንድ ወልዳ ስሙን አበዛችው /2/

አንዱ ሀገር ስትሄድ አማኑኤል አለችው

አንዱ ሀገር ስትሄድ ኢየሱስ አለችው

አንዱ ሀገር ስትሄድ አንድዬ አለችው

ለመናኒው ጸሎት ልዩ እጣን

የዋሻው ሻማ ነሽ እመብርሃን

መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን

ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን

ትርቢኝማለሽ ምን ልሁን

ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሻል

የያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል

የእግዚአብሔር ድንኳን የሚሉልሽ

እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ /2/

ቤቴልሔም ስሔድ አይሻለሁ

ቀራንዮ ስሔድ አይሻለሁ

ፍጹም አትለይም ከልጅሽ

የአንቺስ ልዩ ነው ፍቅርሽ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening