ጠቅላላ

General

ትህትናሽ ግሩም ነው

Lyrics

ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም /2/

እናቱ ሆነሻል ለመድሃኒዓለም /2/

ንጽህት ስለሆነሽ እመቤቴ /2/

እንከን የሌለብሽ እመቤቴ

የፍጥረታት ጌታ እመቤቴ

ባንቺ ያደረብሽ እመቤቴ

የድንግል መመረጥ እመቤቴ

ዜናው አስገረመኝ እመቤቴ

እሳቱን ታቀፈች እመቤቴ

የማይቻለውን እመቤቴ

ምርኩዜ ልበልሽ እመቤቴ /2/

ጥላ ከለላዬ እመቤቴ

ጋሻዬ ልበልሽ እመቤቴ

የኔ መመኪያዬ እመቤቴ

በዓለም እንዳልጠፋ እመቤቴ

ሕይወቴ መሮብኝ እመቤቴ

እንደ ወይን አጣፍጪው እመቤቴ

ድንግል ድረሽልኝ እመቤቴ

የምስራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ /2/

የሁላችን ተስፋ እመቤቴ

እሙነ ፀሐይ ጽድቅ እመቤቴ

የሁሉ ጠባቂ እመቤቴ

ድንግል የድል አክሊል እመቤቴ

ድንግል የጽድቅ ስራ እመቤቴ

ድንግል መሰላል ነሽ እመቤቴ

የተዋህዶ ተስፋ እመቤቴ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening