ጠቅላላ

General

ገድሉ ተዓምራቱ

Lyrics

ገድሉ ተዓምራቱ እጅግ ብዙ ነው

ጣኦትን አዋርዶ የተሸለመው

የተዋህዶ ኮከብ ተክለ ሐዋርያ

አባ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ

ዳግማዊ ዮሐንስ ጠፍር የታጠቀ

ንጹህ ባህታዊ ጠላት ያስጨነቀ

የጸጋ ዘ አብ ፍሬ ዛፍ ሆኖ በቀለ

በደብር ሊባኖስ መናኝ አስከተለ

ደካማ መስሏቸው በአንድ እግሩ ቢያዩት

ባለ ስድስት ክንፉ ተክልዬ የእኛ አባት

እርሱስ አንበሳ ነው ትናገር ደብረ አስቦ

ሌጊዮን ሲዋረድ እፍረት ተከናንቦ

ከካህናት መካከል ሕሩይ ነው ተክልዬ

መጣሁ ከገዳምህ ልሳለምህ ብዬ

ኢትዮጵያዊው ቅዱስ አባ ተክለሃይማኖት

ወልድ ዋህድ ብለህ ምድሪቷን ቀደስካት

የባረከው ውሃ የረገጥከው መሬት

ገላው ያረፈበት ሆኗል ጸበል ዕምነት

ኑና ተመልከቱ ድውያን ሲፈቱ

ይሰብካል ተክልዬ ዛሬም እንደ ጥንቱ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening