✦
ጠቅላላ
•General
ክብረ ቅዱሳን
Lyrics
ክብረ ቅዱሳን ይዕቲ /2/ ክብረ ቅዱሳን /2/
ሙዳየ መና ግሩም ሙዳየ መና /2/
የቅዱሳኑ ክብር ነሽና
እንሰጥሻለን ቅኔ ምስጋና
የወለድሽልን የሕይወት መና
ዝናብ ያለብሽ ታናሽ ደመና
ትህትና ልብስሽ ፍቅር ውበትሽ
ጽንስ የዘልላል ሰላምታ ድምፅሽ
እሳቱን ወልደሽ እሳት ታቅፈሻል
ሳንዘምርልሽ መቼ ይመሻል
የፀሐይ መውጫ ምስራቅ ሆነሽ
ታላቁን ብርሃን አየንብሽ
አትጨልምም ሕይወታችን
ልጅሽ እስካለ ፀሓያችን
ሰዓሊለነ ሰላም ለኪ
ተማህጸነ በኪዳንኪ
ንኢ ርግብየ ምስለ ወልድኪ
ሰማይ ወምድር ይወድስኪ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.