ጠቅላላ

General

እመቤቴ ማርያም

Lyrics

እመቤቴ ማርያም እመቤቴ /2/

ባንቺ ያደረብሽ የሠራዊት ጌታ

እመቤቴ ማርያም ይድረስሽ ሰላምታ /2/

ሕይወቱን የሰጠ ፍጹም ለሰላም

ሁሉንም የሚችል ያለ በአርያም

የአምላክ ማደሪያ ድንግል ማርያም /2/

ጌታ የመረጠሽ እስከ ዘለዓለም /2/

የምድር ባለ ጸጎች ሲማልዱ ፊትሽ

የሰማይ መላዕክት ምስጋና ያቅርቡልሽ

አህዛብ ይንበርከክ ለሃያሉ ልጅሽ /2/

ክብር ይገባሻል በእናትነትሽ /2/

ላንቺ ሲያስተላልፍ ገብርኤል ሠላምታ

ከልዑል ተልኮ ከሠራዊት ጌታ

ሰላም ላንቺ ይሁን ብሎ ያበሰረሽ /2/

እመቤቴ ማርያም ምስጋና ይድረስሽ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening