ጠቅላላ

General

እቴ ሙሽራዬ

Lyrics

እቴ ሙሽራዬ ሰሎሞን ያለሽ /2/

እኔም ልበልሽ እናቴ እመ አምላክ/ማርያም/ ጊቢ በቤቴ /2/

ሁሉም ሰው ለራሱ ወንበር ሲዘረጋ

የክብርን ሽልማት ለራሱ ሲያስጠጋ

ድንግል እንደ ባሪያ ውሃ ተሸክመሽ

ጌታን በትህትና ታገለግያለሽ

ወርቀ ዘቦ ለብሰው በቤቱ ከሞሉት

በሀርና በእንቁ ከተንቆጠቆጡት

በሰው ፊት ያማሩ ብዙ ሆነው ሳለ

ጌታ ግን ወደደሽ እናቴ ነሽ አለ

አሳድጐሽ ሳለ መልአኩ መግቦ

ተሸልመሽ ሳለ በዝቶልሽ ተውህቦ

እጅግ በትህትና ስላገለገልሽው

እንደ ኪሩብ መላዕክ ጌታን ተሸከመሽው

የባሪያውን ውርደት ተመልክቷልና

ለወለድሽው ንጉስ ይድረሰው ምስጋና

ከልብ የወጣ እንጂ ከንቱውን አይደለም

ብጽዕት እንላለን እኛ ዘለዓለም

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening