ጠቅላላ

General

ካንተ የሆነው

Lyrics

ካንተ የሆነው መልካም ነው /2/

ሁሉን በጊዜው ስትሰራው

ካንተ የሆነው መልካም ነው

የኑሃሚን ርስት ሞአብ አይደለችም

ለምለሙን እንጀራ ስቡን ብታበቅልም

በሙላት ወጥታችሁ ባዶ አትመለሱ

የእስራኤልን ቅዱስ ቃልኪዳን አስታውሱ

ሩት አትለፊ የቡኤዝን እርሻ

ጌታ ፈቅዶልሻል የእንጀራሽን ድርሻ

ያለኝ ይበቃኛል ብለው ለሚያምኑት

እጅግ አትርፈዋል ሰላም በረከት

እስማኤል አይደለም የእግዚአብሔር ስጦታ

አብርሃም ሆይ ጽና ባለህበት ቦታ

ሰላም እና ፍቅር ይዞ የሚመጣው

ይስሐቅ ይወለዳል ቢዘገይም ጊዜው

ሰዶም ብታበቅል ለምለሙን ቄጤማ

ለእግዚአብሔር ልጆች መቼም አትስማማ

ድንጋይ እንኳን ቢሆን የአብርሃም ርስት

ጠግበናል ልጆቹ ማርና ወተት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening