✦
ጠቅላላ
•General
እልፍ አእላፋት
Lyrics
እልፍ አእላፋት ወትእልፈት ቅዱሳን ንጹሃን መላዕክት
ቆሙ ለአገልግሎት ጸንተው በአንድነት
ቅዱስ /3/ አምላክ በማለት /2/
ኢዮር ራማ ኤረር የመላዕክት ሀገር
የሐይማኖት የፍቅር የምልክት ክር
እውነት የታየብሽ የመላዕክ ክብር
እንጽና ሲል ገብርኤል በአለንበት ቦታ
በሳጥናኤል ነገድ ነበረ ሁካታ
ግማሹ እየካደ ቀሪው ሲያመነታ
የሳጥናኤል ምኞት እንደ አበባ ረግፎ
ሚካኤል ተሾመ በዕምነት ተደግፎ
ሳጥናኤል ወደቀ ጸጋውን ተገፎ
ቅዱሳን መላዕክት በዕምነት የጸናችሁ
በታላቅ አክብሮት ሰላም እንበላችሁ
ስግደት ወበጸጋ እንስገድላችሁ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.