ጠቅላላ

General

ድንግል መከራሽን

Lyrics

ድንግል መከራሽን ጥቂት ላስታውሰው

በሔሮድስ ዘመን ፍጥረት ያለቀሰው

አንቺ የአምላክ እናት ደግሞም እመቤት

እንደ ችግረኛ ተነሳሽ ስደት

ኧረ ለመሆኑ እንዴት አለቀልሽ

ስትንከራተቺ በረሃን አቋርጠሽ

ይገድሉታል ብለሽ ለልጅሽ አስበሽ

በግብፅ በረሃ መከራሽን አየሽ /2/ መከራሽን

አዛኝቷ ማርያም በጠራሁሽ ጊዜ

እንድትደርሽልኝ በመከራ ጊዜ

መከራን ያየ ሰው መቼም አይጨክንም

አትጨክኝብኝ አደራሽን ማርያም /2/ አደራሽን

አቤት የዚያን ጊዜ ያየሽው መከራ

ያለቀስሽው ለቅሶ ጭራሽ አይወራ

የአማኑኤል እናት አንቺ መከረኛ

እድሜሽን ጨረስሽው ሆነሽ ሀዘንተኛ /2/ ሀዘንተኛ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening