✦
ጠቅላላ
•General
ኢትዮጵያ ሆይ
Lyrics
ኢትዮጵያ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ /2/
ከህዝብሽ ጋር እልል በይ /3/
እጆችሽን በበረከት ስለሞላ /2/
ስላዳነሽ በጭንቅ ቀን ከሞት ጥላ /2/
እግዚአብሔር ብርሃንሽ ስለሆነ /2/
ከአስፈሪው ቀን ልጆችሽን ስላዳነ /2/
ኢትዮጵያ ሆይ እግዚአብሔርን አመስግኚ /2/
በሽብሻቦ እልል በይ /2/
በሽብሻቦ ለአምላክሽ ዘምሪለት /2/
ስብራትሽን ይጠግናል በምህረት /2/
ለህዝብሽም እግዚአብሔር ኃይላቸው ነው /2/
በስቃይሽ የጎበኘሽ መመኪያቸው /2/
ሕዝብህን ባርክ ለዘለዓለም ጠብቃቸው /2/
በጽድቅህም ከፍ አድርጋቸው /2/
የምስጋና ነጎድጓድ ከአፍሽ ይውጣ /2/
ድሮም ቢሆን እግዚአብሔር ነው ያንቺ ዕጣ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.