ጠቅላላ

General

ቅዱስ ሚካኤል

Lyrics

ቅዱስ ሚካኤል /3/ ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ

ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ /2/

አንተ ስለሆንክ ሚካኤል

የአምላክ ባለሟል ሚካኤል

ልመናህ ፈጥኖ ሚካኤል

ከአምላክ ያቀርባል ሚካኤል

የዋህ መላዕክ ነህ አዛኝ ለሰው

ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው /2/

ደዌ የጸናበት ሚካኤል

ባንተ ይድናል ሚካኤል

በአደባባይህ ሚካኤል

ምስክር ሆኗል ሚካኤል

ከቤትህ መጥቶ የተማጸነ

በቃል ኪዳንህ ሕይወቱ ዳነ /2/

ከአምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል

ክብርህ ያበራል ሚካኤል

ለጎስቋላው ስው ሚካኤል

መጠጊያ ሆኗል ሚካኤል

ትልቅ ትንሹ ድሃው ሐብታሙ

ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ /2/

በብሉይ ኪዳን ሚካኤል

ከአምላክ ተልከህ ሚካኤል

ህዝበ እስራኤልን ሚካኤል

ነፃ ያወጣህ ሚካኤል

በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ

በተዓምራትህ ትፈውሳለህ /2/

ባለመድሃኒት ሚካኤል

ያቃተውን ሚካኤል

ፈዋሽ ጸበልህ ሚካኤል

ሆኖኛል ኃይል ሚካኤል

እንደ መጻጉ ድህነት አገኘሁ

ፈውሰኸኛል ባንተ ተመካሁ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening