✦
ጠቅላላ
•General
እንበረታለን ገና
Lyrics
እንበረታለን ገና በጸጋው ተደግፈን /2/
ወልድ ዋህድ እያልን ዓለምን እንከድናለን /2/
ጴጥሮስ የመሰከረው ዓለት ነው መሠረቱ
የአባቶቻችን አምላክ የዋጀን በስቅለቱ
ሲጠብቀን ይኖራል ከወጣንበት ቦታ
እናመልካለን እርሱን በፍቅር በደስታ /2/
ሲገሉን ሲያሳድዱን በቁጥር እንበዛለን
ሲንቁን ሲያዋርዱን በስሙ እንከብራለን
የሲኦልም ደጆች አይችሉንም እኛን
የተክለሃይማኖት አምላክ ይችላል ሊያድነን /2/
ልፋታችንን ያያል የሰማይ አምላካችን
ብዙውን እየሰጠን ጥቂቱን እንወስዳለን
ጽኑ ነው ማይተባችን ሳይበጠስ ይኖራል
የምናመልከው አምላክ በልባችን ይሰራል /2/
ተመስገን አምላካችን ዛሬ በዛን በፊትህ
በአህዛብ ተራሮች ላይ ይመሰገናል ስምህ
እያለፍን በጽድቅህ ዓለምን ልናቀና
ጌታ ሆይ ቅደምልን ቃልኪዳን አለህና /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.