✦
ጠቅላላ
•General
በዕምነታቸው
Lyrics
በዕምነታቸው ዳኑ ከዚያ ነበልባል /2/
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /2/
ናቡከደነጾር ጨካኙ ንጉስ
በባቢሎን ሀገር ጣኦት የሚያነግስ
ወጣቶች ተነሱ በቅናት መንፈስ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /2/
ላሰራኸው ጣኦት አንሰግድም እያሉ
በመንፈስ ቅዱስ ሐይል ልባቸውን ሞሉ
አናንያ አዛርያ ሚሳኤል /2/
እንደ ሦስቱ ህፃናት በዕምነት ለሚቆመው
መለዓኩን ይልካል እግዚአብሔር ሊረዳው
ገብርኤል /2/ ከልኡል /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.