ጠቅላላ

General

እጠበኝ ቆሽሻለሁ

Lyrics

እጠበኝ ቆሽሻለሁ አምላኬ በድያለሁ

ያለ እናት ያሳደግከኝ ያለ አባት የጠበቅከኝ

ያን ሁሉ ዛሬ ረሳሁ እጠበኝ ቆሻሻለሁ /2/

ከድንኳንህ ብታስገባኝ ሞገስ ሰጥተህ

የአፍኒንን ምግባር ይዤ አስቀየምኩህ

ቅባ ሜሮን ያተምክበት ልጅነቴ

እንዳይጎድፍ ጠብቅልኝ ቸር አባቴ

ኃይል አኑረህ እንደ ሶምሶን በፀጉሬ

ጎልያድን አስጥለኸኝ በጠጠሬ

አቅም ቢያንሰኝ በስጋ ጦር ተሸንፌ

ደጅህ መጣሁ የእንባ መባ በዓይኔ አቅፌ

እንዳትረሳኝ በመዳፍህ ቀርጸኸኛል

እንዳትተወኝ ያለ መጠን ወድደኸኛል

ባትሰነዝር ልትቀጣኝ የሞት በትር

የትዕግስትህ ሰሌዳ ነው ለኔ ክብር

ከከንፈሬ ጥበብ ጽፈህ ቅኔ ሲፈስ

በመታበይ አሳዘንኩት ያንተን መንፈስ

ፍቅር ግተህ በእቅፍህ ሥር ያሳደግከኝ

እባክህን በበደሌ አትቅሰፈኝ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening