✦
ጠቅላላ
•General
ተመስገን እንበል
Lyrics
ተመስገን እንበል ተመስገን /2/
በድል አሳልፈህ ያንን ዘመን
አሳይተኸናል ይህን ተመስገን
ጀርባችን ቢቆስልም በዱላቸው
ተገልጦ ባያልቅም መዝገባቸው
የጠራን በደጁ ተከለን
ዓይናቸው እያየ ባረከን ተመስገን
መቼ ነው እያልን ናፍቀን ነበር
ንጋትና ጀንበር ስንቆጥር
ይኸው ሞት በቃል ታረደና
ልባችን ታመነ በአንተ ጸና ተመስገን
ግብፅን ጥለን ወጣን ሲኦልን
ባህሩን ተሻገርን እሳቱን
ኢያሪኮም ፈርሷል በዝማሬ
ነገም ድሉ ያንተ ነው እንደ ዛሬ ተመስገን
ጨለማው አለፈ ፀሐይ ወጣ
ጠላት ተሸነፈ ሃይሉን አጣ
ጌትነት ውዳሴ ክብር ማዳን
በዙፋኑ ላለው ለእርሱ ይሁን ተመስገን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.