ጠቅላላ

General

ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው

Lyrics

ጌታ ብርሃኔና መድሃኒቴ ነው /2/

የሚያስደነግጠኝ የሚያስፈራኝ ማነው /2/

አያሳስበኝም የሳኦል ጥላቻ

ልቤ አይደነግጥም በጎልያድ ዛቻ

የምታመንበት ስሙ ጋሻዬ ነው

ኃይልና ብርታቴ ጌታ ጉልበቴ ነው

ሞገስ ይሆነኛል በነገስታቱ ፊት

እመሰክራለሁ ስሙን ያለ ፍርሃት

አያስጨንቀኝም ሞትና መከራ

ሁሉን የሚችለው አለ ከእኔ ጋራ

ጻድቃንን በገዳም የሚያበረታቸው

ሰማዕታትን በደም እንዲህ ያጸናቸው

አሁንም ይሰራል የብረሃን ጌታ

ስሙን ተሸክሞ በዕምነት ለበረታ

ከስም ሁሉ በላይ የሚበልጥ ስም ይዟል

የማመልከው አምላክ ከሁሉም ይበልጣል

ምንስ እሆናለሁ ስሙን ተደግፌ

በኢየሲስ ክርስቶስ ጥላ ሥር አርፌ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening