ጠቅላላ

General

በጌቴ ሰማኔ

Lyrics

በጌቴሰማኔ በአታክልቱ ቦታ/2/

ለኛ ሲል ጌታችን በዓለም ተንገላታ /2/

አዳምና ሔዋን ባጠፉት ጥፋት /2/

እኛም ነበረብን የዘለዓለም ሞት /2/

መስቀል ተሸክሞ ሲወጣ ተራራ /2/

ይገርፉት ነበረ ሁሉም በየተራ /2/

በአምላክነቱ ሳይፈርድባቸው /2/

እንዲህ ሲል ጸለየ አባት ሆይ ማራቸው /2/

በረቂቅ ስልጣኑ ሁሉን የፈጠረ /2/

በሰው እጅ ተገርፎ ሞተ ተቀበረ /2/

ድንግል አልቻለችም እንባዋን ልትገታ /2/

እያየች በመስቀል ልጇ ሲንገላታ /2/

ፍቅሩን የገለጸው ተወልዶ በስጋ /2/

ኢየሱስ ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening