ጠቅላላ

General

አልፋና ኦሜጋ

Lyrics

አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪ የሆንክ

በከሐዲዎች እጅ ተይዘህ ቀረብክ

ተገፋህ ተደፋህ በጥፊ ተመታህ

እየደበደቡህ ክርስቶስ ሆይ አሉህ

ጽድቅን ስለሰራህ በወንጀል ከሰሱህ

ለአዳም ቤዛ ብለህ ብዙ ተንገላታህ

ቅድሳት እጆችህ የፊጥኝ ታስረው

እንደበግ ተጎተትህ ብትምራቸው

የትም ቦታ ያለህ ሁሉን የምታውቅ

ፊትህን ሸፈኑህ ለመመጻደቅ

በአውደ ምኩራብ ከጲላጦስ ዘንድ

አሳልፈው ሰጡህ አጋልጠው ለፍርድ

ከሐና ቀያፋ ከመሳፍንቱ ደጅ

ከነሔሮድስ ዘንድ አቀረቡህ በአዋጅ

ግርፋት ሕማሙ አልበቃ ብሎህ

በመስቀል ላይ ልትውል ተፈረደብህ

ሳዶርና አላዶር ዳናትና አዴራ

ተፈልገው መጡ ለችንካር በተራ

አምስቱ ችንካሮች ቅንዋት መስቀል

ወገኖችህ መጡ ሥጋህን ለማቁሰል

የሰላም ባለቤት ደረትህ ተወጋ

ሊያያዝ በችንካር እጅህ ተዘረጋ

ምራቅ ተፋብህ ራስክን ሊጎዱ

ግፈኞች አይሁዶች ባንተ ላይ ቀለዱ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening