ጠቅላላ

General

ጌታዬ ሆነህ

Lyrics

ጌታዬ ሆነህ ደም ግባት አልባ

ጀርባው በጅራፍ ስለኔ ደማ

የኔን መገረፍ እርሱ ተገርፎ

ክብር አለበሰኝ እርሱ ተገፎ /2/

በሀሰት ሸንጎ ወጥመድ ተጠምዶ

ጌታ ተያዘ ሕይወቴን ፈቅዶ

ክፉዎች ቢያዩት እንደ ወንበዴ

ለእኔ ግን ሆኗል መውጫ መንገዴ /2/

ታስረሃን ስለኔ ኢየሱስ መድህኔ /2/

ሲዘብቱበት ምራቅ ሲተፉ

የማይደፈር ደፍረው ሲዘልፉ

በከበቡት ፊት ቃል ከለከለ

እኔ እንድናገር እርሱ ዝም አለ /2/

ተወጋህ ስለኔ ኢየሱስ መድህኔ /2/

ሕይወት መንጭቷል ተወግቶ ጎኑ

ለከሳሾቹ ተርፏል ማዳኑ

እጅ እግሩን ሚስማር ሲቸነክረው

የሞትን እሾህ ከእኔ ነቀለው /2/

ተወጋህ ስለኔ ኢየሱስ መድህኔ /2/

እርቃኑን ሆኖ ፈተው ልብሱን

በምህረቱ ጠል ነፍሴን አርክቶ

አለመለመኝ እርሱ ተጠምቶ /2/

ተጠማ ስለኔ ኢየሱስ መድህኔ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening