ጠቅላላ

General

የህያዋን አምላክ

Lyrics

የህያዋን አምላክ ሙታን ሊያስነሳ

በእኩለ ሌሊት ክርስቶስ ተነሳ /2/

ሙታን አይደለንም ክርስቶስ ተነሳ

ህያዋን ነን እኛ ክርስቶስ ተነሳ

በመስቀል ያዳነን ክርስቶስ ተነሳ

ከሃጢያት ቁራኛ ክርስቶስ ተነሳ

የተዋረድነውን ክርስቶስ ተነሳ

ሊያከብረን ዳግመኛ ክርስቶስ ተነሳ

ሞትን አሸንፎ ክርስቶስ ተነሳ

ተነሳልን ለእኛ ክርስቶስ ተነሳ

እናንተስ አትፍሩ ክርስቶስ ተነሳ

እመክራችኋለሁ ክርስቶስ ተነሳ

የተሰቀለውን ክርስቶስ ተነሳ

እንድትሹ አውቃለሁ ክርስቶስ ተነሳ

ህያዋን ከሙታን ክርስቶስ ተነሳ

ለምን ፈለጋችሁ ክርስቶስ ተነሳ

እንደተናገረ ክርስቶስ ተነሳ

ተነስቷል ጌታችሁ ክርስቶስ ተነሳ

ክርስቶስ ሲነሳ ክርስቶስ ተነሳ

በእኩለ ሌሊት ክርስቶስ ተነሳ

አስቀድሞ ታየ ክርስቶስ ተነሳ

ለመቅደላዊት ክርስቶስ ተነሳ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening