✦
ጠቅላላ
•General
በማህፀን ቅኔ
Lyrics
በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
ከተራራማ ሀገር በኤፍሬም ከተማ
ዮሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው
የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሐሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ
በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈጸም በሆድዋ ሲነግስ
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ
ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መች ቻለች ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
ከእናቱ ማህፀን ድምፅን አሰማና
የዮሐንስ እናት ኤልሣቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝላት
ድምጿን ከፍ አረገች ዓለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.