ጠቅላላ

General

ይበራል በክንፉ

Lyrics

ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው

የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው

ያሳደገኝ መልዓክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /2/

ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ

እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ

ዛሬ ላለሁበት ብርቱ ጉልበት ሆነኝ

ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ

በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ

አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ

የሕይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከእርሱ ጋራ

ተጽፏል በልቤ የሚካኤል ስራ

በዚሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሶሶውን

ጽድቅ እየመገበ አሳደገኝ ልጁን

የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ

እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ

ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር

ይሰማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር

የወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ

ታላቁን በረከት በውስጤ አፈሰሰ

ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ

መራኝ ወደ ሕይወት መዳኔን ወደደ

የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ

በጸጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening