ጠቅላላ

General

ዘምር ዘምር አለኝ

Lyrics

ዘምር ዘምር አለኝ ልቤ ተነሳሳ /2/

የአምላኬን ቸርነት እንዴት ብዬ ልርሳ

ያደረገልኝን እንዴት ብዬ ልርሳ

የሚቃጠለው ስብ በፊትህ ምንድን ነው

ሰማይና ምድር ሁሉ ገንዘብህ ነው

ያለኝን ሰብስቤ ባኖረው ከፊትህ

ዋጋ አይሆንም ጌታ ስለ ቸርነትህ

ይበዛል ይሰፋል የእግዚአብሔር ምስጋና

አይቆምም በዘመን ማዕበል ነውና

እንኳን ድንጋይ ቀርቶ ጋራው ቢናድብኝ

የከንፈሬን ፍሬ ማንም አይወስድብኝ

የጳውሎስ የሲላስ መከራ ቢጸና

አልተውም ቅኑውን የአምላክን ምስጋና

ሊያስጥለኝ አይችልም እስር ሰንሰለት

አለብኝ ውለታ የሰማዩ አባት

የተደረገለት ብዙ የተቀበለ

ይኖራል በፍቅሩ እየተቃጠለ

ክብሬን ሁሉ ትቼ ልዘምርልህ

ይህ ነው ችሎታዬ ላንተ የምሰጥህ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening