ጠቅላላ

General

አንድ አድርገን

Lyrics

አንድ አድርገን ጌታ ሆይ አንድ አድርገን

ሰላምህን ፍቅርህንም ለግሰን

ቤተ ክርስቲያን ሆይ ምነው ተረበሽ

አንድነትሽ ጠፍቶ ሰላምን አጣሽ

አንደኛው ሲጠቅምሽ ሌላኛው ሲጎዳሽ

ብዙ ልጆች ወልደሽ የወላድ መካን ሆንሽ

በዘርና ጎሳ ስንከፋፈል

ቅጥራችን ፈረሰ በጠላታችን

መሳለቂያ ሆነን በየአደባባዩ

ልዩነትን አይተው ብዙዎች ተለዩ

ላያችን የሚያምር ልስን መቃብሮች

አስመስለን ያለን የሀሰት አማኞች

በመካከላችን ፍቅርን አስወጥተን

እንደ ርብቃ ልጆች እንገፋፋለን

ለዕምነት ያልቆመው በውሸት ሲከሰን

አንድነት ሳይኖረን ዘመንን አስቆጠርን

ያ ጥቅም ፈላጊው ሰምን እያጠፋ

ለስጋው የሚሆን ርስቱን አሰፋ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening